top of page

የህዝብ ዑደት እና የቤተክርስቲያን ምርቃት

ቅዳሜ፣ ኦገስ 23

|

2135 Sutter St, San Francisco, CA 94115, USA

ከቤይ ኤርያ አካባቢ የተውጣጡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ህዝባዊ ዑደት እና የአዲሱ ቤተክርስቲያን ምርቃት። ኑ ወደ Polk street አብረን እንሂድ ወደ አዲሱ ቤተክርስቲያን አብረን እንግባ!

የህዝብ ዑደት እና የቤተክርስቲያን ምርቃት
የህዝብ ዑደት እና የቤተክርስቲያን ምርቃት

Time & Location

ኦገስ 23 2025 ጥዋት 11:00 – 3:00 ከሰዓት

2135 Sutter St, San Francisco, CA 94115, USA, 2135 Sutter St, San Francisco, CA 94115, USA

About the event

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።


“ከፊተኛው ይልቅ የዚህ የሁለተኛው ቤት ክብር ይበልጣል በዚያም ሰላምን እሰጣለሁ። ትንቢተ ሐጌ ምዕራፍ 2፣ ከቁጥር 9"



ታላቅ የቤተክርስቲያን ምረቃ እና የንግሥ በዓል!


በሰሜን ካሊፎርንያ ሰንፍራንሲስኮ ከተማ እና አከባቢዋ እንዲሁም በመላው አለም የምትገኙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች እንኳን ደስ አላችሁ ።


 በሳንፍራንሲስኮ ከተማ ብቸኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሆነው የደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ላለፉት 11 አመታት በኪራይ ሲገለገልበት ከነበረበት የእግዚአብሔር ጊዜው ደረሰና የእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት እረድቶን የሰማቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል አድራጊነት አግዞን፣ በደብሩ ሰበካ ጉባኤ አቅጣጫ ሰጪነትና ክትትል በህንፃ ኮሚቴው ብርቱ ጥረት በደብሩ አገልጋይ ካህናት፣ ዲያቆናት እና ምዕመናን እርብርብ፣


በቤይ ኤርያ ያሉ አድባራት እና ምዕመናን ተሳትፎ እንዲሁም በመላው ሰሜን አሜሪካ የምትገኙ አብያተ ክርስቲያናትና ምዕመናን ልገሳ በቁርጥ ቀን ደራሾች ኢትዮጲያውያን እና ኤርተራውያን ልዮ ድጋፍ አዲስ ወደተገዛው 1300 ፓልክ እስትሬት(Polk street san Francisco california )ወደሚገኘው አዲሱ ቤተክርስቲያን ነሃሴ 17 ከጠዋቱ 5 / 11am ጀምሮ ልክ እንደ ጥምቀት በዓል በዝማሬ፣ በእልልታ በሽብሸባ ፣ በበገና በእንቢልታ እና በሆታ በአማረ ህብረ ቀለማት ባጌጡ ህዝበ ክርስቲያናት ታጅቦ ከተማውን ዞሮ ሊገባ ነውና እንኳን ደስ አላችሁ!


አዲሱ ቤተክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ የሰሜን ካሊፎርንያ ኔቫዳ እና አሪዞና ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የገዳማት እና ደብራት አስተዳዳሪዎች የአከባቢው ሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን እና ከተለያዩ ከተሞች በተጋበዙ አገልግሎት ስጪ ሚዲያ እና ተጋባዠ እንግዶች በተሰበሰቡበት ተባርኮ ታቦተ ህጉ በክብር ወደ አዲሱ ቤተ መቅደስ ይገባል።



በየትኛውም እስቴት ያላችሁ የሳንፍራንሲስኮ ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያ ከተመሰረተ ጀምሮ ያገለገላችሁ የተገለገላችሁ ለአዲሱ ቤተክርስቲያን ግዢ በፀሎት ፣በገንዘብ፣ በእውቀት፣ በጉልበት የተራዳችሁ በተለያየ መንገድ የደከማችሁ የውጣችሁ የወረዳችሁ በእንባ ስእለት የተሳላችሁ በሙሉ


“ ኑ ወደ Polk street አብረን እንሂድ ወደ አዲሱ ቤተክርስቲያን አብረን እንግባ።


ቅዳሜ ነሐሴ 17/2017 ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት ( Aug 23 11:am )


በማግስቱ እሁድ ነሐሴ 18/2017 ከሌሊት 8:00 Am , Aug 24 (2:00 Am) ጀምሮ በማሕሌት ፣በኪዳን በቅዳሴ እና በዝማሬ የአእናታችንን ቅድስት ኪዳነምህረት በዓለ ንግስ በድምቀት ይከበራል።


ኑ አብረን እግዚአብሔር የገለጠልንን ይህንን ሚስጥር እንይ።


ወስብሐት ለአእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!

Share this event

Event Info: Events

የቅጂ መብት ©2025 በቅዱስ ጊዮርጊስ EOTC. ሁሉም መብቶች የተጠበቁ ናቸው።

  • Facebook
  • Instagram
  • YouTube
bottom of page