top of page
ስለ እኛ

ታሪክ
የሳንፍራንሲስኮ ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዶግማና ቀኖና መሠረት ሐምሌ 12/2006 ዓ.ም በእግዚአብሔር በአምላካችን ቅዱስ ፍቃድ በብጹእ ወቅዱስ አቡነ ፋኑኤል ቡራኬ ተመሠረተ።
እሴት
-
የእግዚአብሔርን ቃል ለትውልድ ሁሉ ማዳረስ እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ ላይ የተመሰረተ እና በሥነ ምግባር የታነጸ ማህበረሰብን ማሳደግ።
-
ሁለንተናዊ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን መስጠት፣ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባርን ለልጆች ማስተማር እና እምነትን ለትውልድ ማስተላለፍ።
-
በሥነ-መለኮታዊ እውቀት እና በመንፈሳዊ ፀጋ ምዕመናንን ለነፍስ ድሕነት ማዘጋጀት።


ራዕይ
የደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኪዳነ ምሕረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ራዕይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናን የተዋሕዶ እምነትን እና ትውፊትን ጠብቀው ሲያድጉ ማየት ነው። እንዲሁም እግዚአብሔርን በሙሉ ልብ ለማምለክ፣ መለኮታዊ ፈቃዱን ለመፈፀም እና ኢ-አማንያንን ወደ ሀይማኖታችን ለመሳብ እንጥራለን።
bottom of page